የአዲስ አበባ የቤት ዋጋ 2012 ,2013 ለምን አሻቀበ ?

ውሎ ማደሩ በጸጋው መልካም ሆኖ ሳለ የቤት ሽያጭ ዋጋ ወር በወር ዋጋው እየጨመረ ነውና ለምን ብሎ መጠያቁ አስፈላጊ ነው።

 እኛም ያወቅነውን   የተገብዘብኩትን  አንዲሁም እይታችንን ብናካፍላችሁ ብለን ነው የዛሬ ካለን አመታዊ ክንውን ውስጥ ለምን ብለን ያሥብነውን እንደ ሻጭ ሳይሆን   አንደገዥ ሆነን  የየነውን የታዘብነው የአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ማሻቀብ ምክኒያቱ ምንድን ነው? በጥቂቱ  እንመልከትው

 እንደምሳሌ ለመጥቀስ ቦሌ ቡልቡላ 175 ካሬ  ቪላ ቤት 5.8 ሚሊያን ብር ይሸጥ ነበር  ከአመት በፊት አሁን በ50% አድጎ  9 ሚሊዮን ብር እየተሸጥ ነው    ለምን ?

የዛሬ 10 ወር 26 ሺ /ካሬ  ሲሸጥ የነበር የሪል እስቴት አፓርታማ አሁን 50% አድጎ  40_50 ሺ  እየተሸጠ ነው  ። ለምን ?

ይህ ከላይ የተጠቀሰው ዋጋ መሀል ከተማ የሚሸጥ የሪል እስቴት አፓርታማን  ዋጋ አይጨምርም

                   አምስቱ  የቤት ዋጋ የማናሪያ ምክኒያቶች

                          1   መንገድ   

የመንገድ ሁኔታ ትራንስፖርት የመገኝት ቀላልነቱ  በግል መኪና  ከሆነ አማራጭ መንገድ ያለው የመኪና መጨናነቅ የማይበዛበት እንዲሆን መፈለግ ነው ።  ይህን ስል በአንጻርዊነት  አዲስ አባባ ውስጥ  ከሉት ሰፈር የተሻለ የሆነውን  ለማለት ነው እንጂ የትርንስፖርትም ሆነ የመንገድ መጨናነቅ የእለት ተለት  የአዲስ አበባ አንድ ገጽታ ከሆነ ሰንብቶል ።

                        2  የሰፈር ሁኔታ

ገዥ ቤት ሲገዛ ቤት ብቻ ሳይሆን ሰፈር እና ጎረቤት እንዲሁም ተመሳሳይይ የንሮ ዳረጃ የለውን ከባቢ ይፈልጋል  ይህ የምርጫ  ጉዳይ መክፈል የሚችለውም መክፈል ያማይችለውም ፍላጎት በመሆኑ  ለዋጋው መናር አስተዋጾ ያረጋል

                        3    ቤት ሰሪዋች 

ቤት ሰሪዎች ሰርተው ለመሸጥ አንድ አካባቢ ላይ ገዝተው በብዛት ሲገነብ አካባቢው ውዲያው ይለወጣል  ይለማል ስለዚህም የአካባቢውን ዋጋ የመወስን ስልጣን ይሰጣቸዋል!!!

በዚህ አጋጣሚ የነጋዴ የስራው ቤት ጥሩ አይደለም የሚባለው አባባል በግሌ የተሳሳተ አባባል  ነው ለማለት እደፍራለሁ   ነጋዴ የሰራው ቤት በልምድም በእውቀትም የዳበር ስለሆነ ፅድት አርገው ነው የሚሰሩት። በውበት ፤በዲዛይ፤ በአጨራረስ ውበት ፤በማቴርያል አጠቃቀም  ወዘተ …  90 % ጎበዝ ናቸው።

 አጥፊ በየትኛውም የሥራ መስክ አይጠፋም  ይህ እንደተጠበቀ  ሆኖ  ማለት ነው ።

                              4 የሰው እርብርብ

የሰው ርብርብ በተመሳሳይ ሰፈር በአስፓልት ግራን ቀኝ የተለያያ ዋጋ ቢኖረውም ልዩነቱን ሳይመዝን ረከስ ባለው አካባቢ የመግዛት ፍላጎቱ   ያነሰ  ነው ስለዚህ  ተገቢ  ያልሆነ  ተጨማሪ ወጭ አውጥቶ ይገዛል ። ብሌላ አነጋገር ለቤት ዋጋ መናር አስተዋጾ እያረጋል ነው ማለት ነው

                            የእቃ መናር

 ዋና ለቤት ዋጋ መጨመር አስተውጾ የየአንዳንዱ እቃ ዋጋ መጨመር ሲሆን ለምሳሌ የንጽህና ቤት እቃ 3ሺ ሲሸጥ የነበርው 8ሺ ብር የሴራሚክ ዋጋ የግራናይት ዋጋ የቆርቆሮ ዋጋ የሲሚንቶ ዋጋ …ወዘተ መወደድ የቀጥታ ዋጋ ጭማሪ አምጥቶል ።

ስለዚህ ከላይ የዘርዘርናቸው ሁሉም የቤት ግዢን ለማናር አስተዋጾ ቢኖረውም    50% የዋጋ መናርን ለመከላከል  አንዲረዳንና  ቢያንስ 25 % ላይ ለመግታት ይህንን እናካፍላቹ   

  •  ብዙ ሰው ጎደኛው ቤተስቡ ያለበትን ሰፈር ነው ቤት መግዛት የሚፈልገው ምንም ይህል ከራሱ ቤተስብ ጋር የሚሄድ  የተስማማ ሰፈር መሆኑን አያረጋግጥም በቅርበቱ ት/ቤት ይኑር አይኑር  የአካል ብቃት ማዘውተሪያ ይኑር አይኑር አያስተውሉም መጀመርያ ክትፎ ቤት ቁርጥ ቤት ካለ ሰፈሩ የልማ ነው ብለው  ነው የሚያስቡት ። ስለዚህ ስው በርሱ ፍላጎት የሚገዛ ከሆነ ስብጥሩ ጥሩ ስለሚሆን ለዋጋ አለመናር አስተዋጽ ያደርጋል  ።
  • በጀት ወሳኝ ነው በራስ ባጀት የሚምጥን ቤትን መመልከት ለምሳሌ ፦ አንድ ሰው 20 ሚሊዮን የሚባልን ቤት የለባጀቱ ሄዶ ከውደደው በሆላ 18 ቢሸጡት ምርጥ ነው የሚል አስተያያት  ሲሰጥ በተዘዋዋሪ በባጀቱ 6 ሚሊዮን  የሆነበት ቦታ ቤት ሊገዛ  ሲሄድ ዋጋ ጨምሮ ያገኘዋል 9 ሚሊዮን ሆነ። ለምን ? ሻጭ ከመሸጡ በፊት ዞሮ ዋጋ የየል የቤቱን ደርጃ ያወጣል በተጨማሪ የበዛው ደላላ  ዋጋ ከምን አንጻር እንደጨመረ  ሳይረዳ ያንተ ቤት 9 ሚሊዮን  የወጣል የሚል አስተያየት ይሰጥሀል ። ስለዚህ ከላይ የአንተ አስተያያት(ገዥ) አንዲሁም  የደላላው አስተያየት አፋዊ ግሽበትን  ያመጣና ይጨምራል ይህ ደሞ አቅም ያለው ገዥ ብቻ መግዛት እንዲቸ ይሆናል ። በለፈለፉ በአፍ ይጠፉ አይደል የሁሉም የአፍ ግሽበት ኢኮኖሚያዊ ቀመር በማይመራት ሃገር ላይ አያንዳንዱ ጠጠር የግሽበቱ አስተዋጾ አለው ።
  • ገዥ ሁሌም ጽድት ያለ ቤት ብቻ ነው የሚፈልገው ይህ ከባድ ስህተተ ነው ቀለም ሳይሆን ቤትን ቤት ያሚያረገው ዲዛይኑ ተስማሚ ነው ወይ  ያገዥውን ቤተስብ ማኖር ይችላላ ቢታደስ ውበቱን  ምን ያህል ማሰብ  ይቻላል  በዚህ አካሄድ ከሄዱ ቢያንስ 1.5 ሚሊዮን ማትረፍ ይቻላል በ5 መቶ ሺ ቤቱን ማደስ ከተቻለ የተጣራ 1 ሚሊዮን ብር ማትረፍ ተቻለ ማለት ነው በሌላው አንጻር  ለግሽበቱ ያለውን አስተዋጾ ይቀነስ ።

                                                                     ሰላም

                                                                                       ኤርሚ ዘ ኢትዮጵያ

About Author

Related Post

1 Comment

  • נערות ליווי בקיסריה

    2 years ago / April 20, 2023 @ 11:46 am

    I was pretty pleased to discover this web site. I want to to thank you for your time for this fantastic read!! I definitely really liked every bit of it and I have you book marked to see new things on your web site.

Leave a Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *